Web Content Display Web Content Display

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት

መግቢያ

ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ባሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ቀውስ ከመሆኑ በላይ በልማት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የተደቀነ ከባድ ፈተና ነው፡፡ ይህ ወረርሽኝ ሀገራችን ከ649 ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ እና የኤች.አይ.ቪ ስርጭት መጠን 0.91% መድረሱን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ባለፉት አመታት አበረታች ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ያለፉት 4 አመታት የመቀዛቀዝ ሁኔታ በመፈጠሩ ቫይረሱ እንደገና የስርጭት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ተጋላጭ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች እና የልማት ተቋማት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ጥናት በማድረግና በመለየት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የሚኒስቴር መ/ቤታችንም ተገላጭ ተብለው ከተለዩት ትላልቅ የልማት ተቋማት አንዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ወረርሽኙ አምራች የሆነውን የሰው ሀይል ጤንነት ከመጉዳት ባሻገር ገቢውን  በማመናመን ምርታማነት እንዲቀንስ የበኩሉን ተፅዕኖ እየፈጠረ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስትና አጋሮቹ እየተስፋፋ የመጣውን የኤች.አይ.ቪ ስርጭት ለመግታት ሁሉም አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ከፍተኛ የቅስቀሳና የህብረተሰብ ንቅናቄ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በ2020 3ቱን 90ዎች ለማሳካት ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ፖሊሲ ተነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡

በ2030 ኤድስን የማቆም ራዕይ ከግብ ለማድረስ አገሮች ስምምነት ተቀብለው በመተግበር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሀገራችንም የሶስቱን ዘጠናዎች በ2020 ለማሳካት ማለትም፡- 90% ኤች.አይ.ቪ በደማቸውየሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ራሳቸውን እንዲያውቁ፣ ተመርምረው ራሳቸውን ካወቁ ሰዎች መካከል 90%ቱ መድሃኒቱን እንዲጀምሩ ማድረግ፣ መድሃኒቱን ከጀመሩት ሰዎች 90%ቱ ጤንነታቸውን ጠብቀው የቫይረሱ መጠን በደማቸው ተዳክሞ በጤና እንዲኖሩ ማስቻል ነው፡፡

በዚህ ምክንያት የበሽታውን ስርጭትና ለመቀነስ፣ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከኤች.አይ.ቪ ነጻ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር የማህበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ሚና ነው! በሚል መሪ ቃል የማህበረሰቡን ሚና በማጉላት እና ለውጥ ለማምጣት የሁሉም ህብረተሰቡ ተሳትፎ የላቀ መሆኑን እና ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ ይገኛል፡፡

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ዘርፍም በርካታ ሰራተኞችን ያሳተፈ ትላልቅ የልማት ግንባታዎችን እና ፕሮጀክቶች የሚያስፈፅም በመሆኑ ሠራተኛው ከቤተሰብ ርቆ የሚኖር መሆኑ እና ተንቀሳቃሽ ሰራተኞች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ልማት ለማካሄድ እንዲቻል የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳይ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ስትራቴጂ ዕቅድ በማካተት ይህንን ለማስፈፀም እንዲቻል ከ1999 ዓ.ም እስከ 2004 ዓ.ም በግብረሀይል ደረጃ እንዲሁም ከ2004እስከ አሁን ድረስ በጽ/ቤት ደረጃ እንዲዋቀር ተደርጎ ችግሩን ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የመ/ቤቱ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ የድጋፍ እንክብካቤ የውስጥ አሰራር መመሪያ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ የጸደቀ ሲሆን ድጋሜ የማሻሻያ ስራዎች ተሰርተው ከመስከረም 2005 ዓ.ም ጀምሮ በሚኒስትሩ ጸድቆ በስራ ላይ ይገኛል፡፡

 1. ዓላማዎች
  1.  በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሴክተር የኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞችን መተግበር፣
  2.  የኤች.አይ.ቪ ምክር አገልግሎቶችን ማጠናከር፣
  3.  የድጋፍና እንክብካቤ ስራዎችን ማጠናከር፣

2.    የበጀት አመቱ ዋና ዋና ግቦች

2.1 የመከላከል የባህሪ ለውጥ ተግባቦት ሥራዎችን መተግበር

2.2 የኮንዶም ስርጭት ማሳደግ፣

2.3 የኤች.አይ. የምክር አገልግሎቶች እንዲሰጡ ማድረግ፣

2.4 የኤች.አይ./ኤድስ ተፅእኖ ለማስወገድ የድጋፍና እንክብካቤ እና የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎን ማጠናከር

3.5  የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ማከናወን ናቸው፡፡

በጽ/ቤቱም የእስካሁን የስራ እንቅስቃሴ እና አሁንም እየተገበራቸው የሚገኙ

 1. ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ የወረደ የጽ/ቤቱ ውጤት ተኮር ዕቅድ ተዘጋጅቶ ለሠራተኞች በማውረድ እየተገበረ ይገኛል፡፡
 2. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጉዳይ እያንዳንዱ ሠራተኛ የራሱ ጉዳይ አድርጎ በመቀበል ወረርሽኙን ለመከላከል ሰራተኛው በፍቃደኝነት በየወሩ ከደመወዝ በሚያዋጣው ገንዘብ የኤድስ ፈንድ በማቋቋም፣ ተመርምረው እራሳቸውን ላወቁና ቫይረሱ በደማቸው ለተገኘባቸው 20 የኤድስ ህሙማን  ሠራተኞች፣ በኤድስ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ 1 ሠራተኛ ቤተሰብ፣ በበሽታው ህይወቷን ላጣች ለሰራተኛ 2 ህጻናት በየወሩ የገንዘብና የስነልቦና ድጋፍ እንዲሁም ቫይረሱ በደማቸው ለሚገኝ የመ/ቤታችን ሰራተኞች ህጻናት ልጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ የገንዘብ ድጋፍ በአመት አንድ ጊዜ ለ1 ልጅ 1000 (አንድ ሺህ ) ብር ጠቅላላ ለ11 ህጻናት 11 ሺ ብር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡
 3. በየጊዜው ባለሙያዎችን በመጋበዝና ስለወቅታዊ ኤች.አይ.ቪ ጉዳይና ስለበሽታው በማስተማር ግንዛቤ የማሳደግ ስራ ተሰርቷል፣ የተለያ ወቅታዊ በራሪ ወረቀቶችን በመበተን፣ ፖስተሮችን በመለጠፍ ሰራተኞች በየኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲገኙ ተደርጓል፡፡
 4. ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖችን በመጋበዝ ስለ ኤች.አይ.ቪ ጉዳዮች የህይወት ተሞክሮ ተሰጥቷል፡፡
 5. ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰራተኞች ለስራ አመቺ ቦታ ሲጠይቁ ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር የተለያየ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡ (ከሰው ሀብት፣ከፋይናንስ እና ከአገልግሎት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ጋር በመነጋገር) ድጋፍ ተደርጓል
 6. የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቀነስ በኮንዶም እንዲጠቀሙ በቋሚነት ከ100 ሺህ በላይ የኮንዶም በእርዳታ በማሰባሰብ የስርጭት ስራ ተሰርቷል፡፡
 7. በውሃ መስኖና ኢነርጂ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በቅንጅት ለመከላከል እንዲቻል በሚኒስቴር መ/ቤቱና በተጠሪ መ/ቤቶች የጸረ.ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የተጠሪ መ/ቤቶች ጥምረት ተቋቁሞ የአፈጻጸሙ መመሪያ ጸድቆ በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
 8. የዓለም ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ትምህርቶችንና መልዕክቶችን በማስተላለፍ ሰራተኛው ግንዛቤው እንዲጨምር ተደርጓል፡፡
 9. ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች የስራ ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል አፈጻጸሙ ይገመገማል፡፡
 10. የጽ/ቤቱን እና የተጠሪ መ/ቤቶችን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ጽ/ቤት ሪፖርት በየሩብ ዓመቱ ይልካል፣ ይገመገማል፡፡
 11. የአቻ ለአቻ ውይይት፣የቡድን ውይይት፣የተጠሪ መ/ቤቶችና የልማት ፕሮጀክቶች ለተውጣጡ ፎካል ባለሙያዎች (HIV/AIDS mainstreaming) ስልጠና በየጊዜው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ በ2030 የተቀመጠው በበሽታው የመያዝ እድልን ወደ ዜሮ የማድረስ ግብ ሊሳካ የሚችለው ማህበረሰቡ፣ በየደረጃው ያለው አመራር፣ ባለድርሻ አካላት፣ ሴክተር መ/ቤቶች እና አጋር ድርጅቶች የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ኤች.አይ.ቪን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ የራሳቸው የሥራ አካል አጀንዳ አድርገው በመውሰድ ወገንን ፣ሀገር እና በተለይ ሴክተራችንን ከዚህ አስከፊ በሽታ ነጻ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባው የሚጠይቅ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የሚኒስቴር መ/ቤታችን ዳይሬክተሮች፣ ጽ/ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት  ወረርሽኙን ለማጥፋት እንደሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት እኛም የበኩላችንን ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

  ያገጠሙ ችግሮች

 • ለክፍሉ ለሜይንስትሪሚንግ ስራዎች በቂ በጀት አለመመደቡ
 • በጅኤጅ በተጠናው መሰረት ሊያሰራ የሚችል በቂ ባለሙያ ባለመመደቡ በአሁኑ ሰዓት ክፍሉ በሀላፊ እና ከአንድ ባለሙያ ውጭ ሌላ አለመኖሩ ተቋሙ ተጋላጭ ከመባሉ አንጻር ለቀጣይ ከላይ ያሉት ችግሮች ካልተቀረፉ አሳሳቢ ችግር መጋረጡን ያሳያል
 • ለክፍሉ የተሠጠው ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑ (ለባለሙያዎች በጅኤጅ የተሰጠው መደብ ዝቅተኛ በመሆኑ የሚያመለክት ሰው አለመኖሩ)

የተወሰደ መፍተሄ

 • ያሉት ሀላፊ እና ባለሙያ በመናበብ ስራዎችን በተቻለ አቅም እየሰሩ መሆኑ
 • ፕሮፖዛል በማዘጋጀት በሚገኘው ገንዘብ መጠን የሚችለውን ያህል እየተሰራ መሆኑ
 • ለሚመለከተው ክፍል በደብዳቤ እና  በአካል በመሄድ የችግሩን ሳሳሳቢነት በማስረዳት የማሳወቅ ስራ የተሰራ መሆኑ ጽህፈት ቤቱ በተለያየ ጊዜ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ካከናዎናቸው ስራዎች መካከል ስልጠናዎች ተሰጥተዋል'